ኢዮብ 4:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ በአገልጋዮቹ እንኳን አይተማመንም፥ በመላእክቱንም ላይ ስሕተት ያገኛል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ በአገልጋዮቹ ላይ እምነት ካልጣለ፣ መላእክቱንም በስሕተታቸው ከወቀሠ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ የማይተማመንባቸው ከሆነ፥ በመላእክቱ እንኳ ስሕተት የሚያገኝባቸው ከሆነ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ አገልጋዮቹንም አይተማመናቸውም፥ መላእክቱንም በጭንቅ ይጠራጠራቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በባሪያዎቹ አይታመንም፥ መላእክቱንም ስንፍና ይከስሳቸዋል፥ |
የመጀመሪያ ቦታቸውን ያልጠበቁትን ነገር ግን መኖሪያቸውን የተዉትን መላእክት በዘለዓለም እስራት እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ከጨለማ በታች ጠብቆአቸዋል።