ነገር ግን ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ጊዜውም የዝናብ ጊዜ ነው፥ በውጭ ልንቆም አንችልም፥ በዚህ ነገር እጅግ ተላልፈናልና ይህ ሥራ የአንድ ወይም የሁለት ቀን ሥራ አይደለም።
ኢዮብ 37:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በረዶውንና ውሽንፍሩን ብርቱንም ዝናብ፦ በምድር ላይ ውደቁ ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በረዶውን፣ ‘በምድር ላይ ውደቅ’ ውሽንፍሩንም ‘ዶፍህን አውርደው’ ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በረዶ በምድር ላይ እንዲወርድ ያደርጋል፤ ብርቱ ዝናብም እንዲዘንብ ያዛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በረዶውንና ውሽንፍሩን፥ ብርቱውንም ዝናብ በምድር ላይ እንዲወርድ ያዝዛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በረዶውንና ውሽንፍሩን ብርቱንም ዝናብ፦ በምድር ላይ ውደቁ ይላል። |
ነገር ግን ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ጊዜውም የዝናብ ጊዜ ነው፥ በውጭ ልንቆም አንችልም፥ በዚህ ነገር እጅግ ተላልፈናልና ይህ ሥራ የአንድ ወይም የሁለት ቀን ሥራ አይደለም።
በሦስት ቀን ውስጥ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመዓቴ በዐውሎ ነፋስ እሰነጣጥቀዋለሁ፥ በቁጣዬም ዶፍ ዝናብ፥ በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ ሊያጠፋው ይወርዳል።
አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ጠፈሩንም በምድር ላይ የመሠረተ፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሰው እርሱ ነው፤ ስሙም ጌታ ነው።