ኢዮብ 32:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ ቃላችሁን በትዕግሥት ጠበቅሁ፥ የምትናገሩትን ነገር እስክትመረምሩ ድረስ ሙግታችሁን አዳመጥሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በምትነጋገሩበት ጊዜ ታገሥሁ፤ ቃላት እየመረጣችሁ ስትናገሩ፣ በጥሞና ሰማኋችሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተ የምታቀርቡትን ምክንያት እጠባበቅ ነበር። ሐሳባችሁን ግልጥ ለማድረግ ቃላት በመምረጥ፥ የምትናገሩትንም አዳምጥ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ንግግሬን አድምጡኝ፤ የምትናገሩትን ነገር እስክትመረምሩ ድረስ እየሰማችሁት እነግራችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ቃላችሁን በትዕግሥት ጠበቅሁ፥ የምትናገሩትን ነገር እስክትመረምሩ ድረስ ብልሃታችሁን አዳመጥሁ። |