ኢዮብ 31:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በእውነተኛ ሚዛን ልመዘን፥ እግዚአብሔርም ቅንነቴን ይወቅ። በሐሰት ሄጄ እንደሆነ እግሬም ለሽንገላ ቸኩላ እንደሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በሐሰት ሄጄ እንደ ሆነ፣ እግሬም ወደ ሽንገላ ቸኵሎ ከሆነ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሐሰት ተናግሬ እንደ ሆነ፥ ሰውንም አታልዬ እንደ ሆነ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፌዘኞች ጋር ሄጄ እንደ ሆነ፥ እግሬም ከመንገዱ ገለል ብላ እንደ ሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእውነተኛ ሚዛን ልመዘን፥ እግዚአብሔርም ቅንነቴን ይወቅ። በሐሰት ሄጄ እንደ ሆነ እግሬም ለሽንገላ ቸኵላ እንደ ሆነ፥ |
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከንቱ ነገርን ስለ ተናገራችሁ፥ ውሸተኛ ራእይንም ስላያችሁ፥ እነሆ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በነፋስና በውሸት የሚሄድ፥ ሐሰትንም የሚናገር፥ “ስለ ወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ስብከት እናገርልሃለሁ” የሚል ሰው ቢኖር፥ እርሱ የዚህ ሕዝብ ሰባኪ ይሆናል።
“የአማልክት አምላክ ጌታ! የአማልክት አምላክ ጌታ! እርሱ አውቆታል፥ እስራኤልም ራሱ ይወቀው፤ በጌታ ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደሆነ ዛሬ አታድነን፤