ኢዮብ 30:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀኜ በኩል ዱርዬዎች ተነሥተዋል፥ እግሬንም ያሰናክላሉ፥ የጥፋታቸውን መንገዶች በእኔ ላይ ይቀይሳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቀኜ በኩል ባለጌዎች ሆ! ብለው ተነሡብኝ፤ ለእግሬም ወጥመድ ዘረጉ፤ የዐፈር ድልድልም አዘጋጁብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስተቀኜ በኩል ስድ ዐደጎች ተነሡብኝ፤ እግሬንም ለማሰናከል ወጥመድ አጠመዱ፤ በእኔም ላይ ከበባ አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኀይሉ ቀኝ ተነሣብኝ፤ እግሮቹንም ዘረጋብኝ፤ የሞትንም መንገድ በእኔ ላይ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀኜ በኩል ዱርዬዎች ተነሥተዋል፥ እግሬንም ይገለብጣሉ፥ የጥፋታቸውን መንገድ በእኔ ላይ ይጐድባሉ። |