ኢዮብ 29:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥሬ በውኃ ላይ ተዘርግተው፥ ጠልም በቅርንጫፌ ላይ ያድር ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥሬ ወደ ውሃ ይዘረጋል፤ ጠልም በቅርንጫፌ ላይ ያድራል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥሮቹ ዘወትር ውሃ እንደሚያገኙና ቅርንጫፎቹም በጠል እንደሚርሱ ዛፍ ነበርኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኃ በሥሬ ላይ ይፈስሳል፥ ጠልም በአዝመራዬ ላይ ይወርዳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥሬ በውኃ ላይ ተዘርግቶአል፥ ጠልም በቅርንጫፌ ላይ ያድራል፥ |
እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥ ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሮቹን እንደሚዘረጋ፥ ሙቀትም በመጣ ጊዜ እንደማይፈራ፥ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም ከማፍራት እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።”