የታላላቅ ሰዎች ድምፅ ይደበቅ፥ ምላሳቸውም ከትናጋቸው ጋር ይጣጋ ነበር።
የመኳንንት ድምፅ ጸጥ ይል፣ ምላሳቸውም ከላንቃቸው ጋራ ይጣበቅ ነበር፤
የአገር መኳንንትም እኔ ባለሁበት ጸጥ ይሉ ነበር፤ ምላሳቸው ተሳስሮ መናገር ያቅታቸው ነበር።
የሰሙኝም ብፁዕ ይሉኛል። ምላሳቸውም በትናጋቸው ተጠጋ።
የታላላቆቹም ድምፅ አረመመ፥ ምላሳቸውም በትናጋቸው ተጣጋ።
ከቃሌ በኋላ አንዳች አልመለሱም፥ ንግግሬም በእነርሱ ላይ ተንጠባጠበ።
ባላስታውስሽ፥ ምላሴ በጉሮሮዬ ይጣበቅ፥ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።
ምላስህን ከትናጋህ ጋር አጣብቃታለሁ፥ አንተም ዲዳ ትሆናለህ፥ እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና የሚገስጽ ሰው አትሆንባቸውም።