ኢዮብ 28:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኦፊር ወርቅ፥ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኦፊር ወርቅ፣ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብ ኦፊር ከሚባል ወርቅና፥ መረግድና ሰንፔር ከሚባሉ ዕንቆች የከበረች ናት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአፌር ወርቅም ጋር አትወዳደርም። በከበረ መረግድና በሰንፔር አትገመትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኦፊር ወርቅ፥ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም። |
በእግዚአብሔር የአትክልት ቦታ በዔድን ነበርህ፤ የከበረ ድንጋይ ሁሉ ልብስህ ነበር፥ ያቁት፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቁ፥ ወርቅ፥ ልብስህ ነበረ፤ የከበሮህና የእንቢልታህ ሥራ በአንተ ዘንድ ነበረ፤ በተፈጠርህበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር።