ሥሩም በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥ ግንዱም በመሬት ውስጥ ቢሞት፥
ሥሩ በምድር ውስጥ ቢያረጅ፣ ጕቶው በመሬት ውስጥ ቢበሰብስም፣
ምንም እንኳ ሥሮቹ በመሬት ውስጥ ቢያረጁ ግንዱም በዐፈር ውስጥ ቢበሰብስ፥
ሥሩም በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥ ግንዱም በጭንጫ ውስጥ ቢሞት፥
“ዛፍ እንኳን ተሰፋ አለው፥ ቢቈረጥ የማቈጠቁጥ፥ ቅርንጫፉም የማደግ እድል አለው።
በውኃ ሽታ ያቈጠቁጣል፥ እንደ አትክልት ቅርንጫፍ ያወጣል።
ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፥ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፥ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።
እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።
አንተ ሞኝ! የምትዘራው ካልሞተ ሕይወት አያገኝም።