ኤርምያስ 49:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዙፋኔንም በኤላም አኖራለሁ ከዚያም ንጉሡንና ሹማምንትን አጠፋለሁ፥ ይላል ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዙፋኔን በኤላም እዘረጋለሁ፤ ነገሥታቷንና መኳንንቷን አጠፋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሣቸውንና መሪዎቻቸውን አጠፋለሁ፤ ዙፋኔንም በዚያ እዘረጋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዙፋኔንም በኤላም አኖራለሁ፤ ከዚያም ንጉሡንና መሳፍንቱን አጠፋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዙፋኔንም በኤላም አኖራለሁ ከዚያም ንጉሡንና አለቆቹን አጠፋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እንዲህም በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባርያዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አመጣለሁ፥ ዙፋኑንም እኔ በሸሸግኋቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም የዙፋኑን ድንኳን በላያቸው ይዘረጋል።
በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን በሚሹአት ፊት ኤላምን አስደነግጣለሁ፤ በእነርሱም ላይ ጽኑ ቁጣዬ የሆነውን ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ እስካጠፋቸውም ድረስ በኋላቸው ሰይፍ እልክባቸዋለሁ፤