ኤርምያስ 44:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስለዚህም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይሁዳን ሁሉ ለማጥፋት ፊቴን ለክፋት በእናንተ ላይ አደርጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣትና ይሁዳን ሁሉ ለመደምሰስ ቈርጬ ተነሥቻለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ በእናንተ ላይ በቊጣ ተነሣሥቼ ይሁዳን በሙሉ እደመስሳለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይሁዳን ሁሉ አጠፋ ዘንድ፥ ፊቴን ለክፋት በላያችሁ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይሁዳን ሁሉ አጠፋ ዘንድ ፊቴን ለክፋት በላያችሁ አደርጋለሁ። |
ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ፊቴን በዚህች ከተማ ላይ አድርጌአለሁና፤ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ትሰጣለች፥ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል፥ ይላል ጌታ።’
ስለዚህ እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ስሙ፤ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ‘ሕያው በሆነ ጌታ እግዚአብሔር እምላለሁ!’ ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ፥ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፥ ይላል ጌታ።
ፊቴን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ከእሳት ቢያመልጡም፥ እሳት ግን ይበላቸዋል፥ ፊቴን በእነርሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
“ከእስራኤልም ልጆች ወይም በመካከላቸው ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፥ ያንንም ሰው ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።
በጠላቶቻቸውም ፊት ተማርከው ቢሄዱ እንኳ ከዚያ ሰይፍን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይገድላቸዋል፤ ዓይኔንም በእነርሱ ላይ ለክፋት እንጂ ለመልካም አላደርግም።”