የሚቃጠለው መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕትን፥ የእህሉንም ቁርባን ዕጣኑንም፥ የምስጋናውንም መሥዋዕት ይዘው ከይሁዳ ከተሞች ከኢየሩሳሌምም ዙሪያ፥ ከብንያምም አገር፥ ከቈላውም ከደጋውም ከደቡብም ወደ ጌታ ቤት ይመጣሉ።
ኤርምያስ 33:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፥ በቈላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በጎቹ መንጋውን በሚቆጥረው ሰው እጅ ሥር እንደገና ያልፋሉ፥ ይላል ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተራራማው አገር፣ በምዕራብ ተራሮች ግርጌና በኔጌብ ባሉ ከተሞች በብንያም አገር፣ በይሁዳ ከተሞች እንዲሁም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች መንጎች እንደ ገና በሚቈጥራቸው ሰው እጅ ሥር ያልፋሉ’ ይላል እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተራራማው አገር በኮረብቶች ግርጌና በይሁዳ ደቡብ ባሉ ከተሞች፥ በብንያም ክፍለ ግዛት፥ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉት መንደሮችና በይሁዳ የገጠር ከተሞች ሁሉ እረኞች እንደገና በጎቻቸውን ይቈጥራሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፥ በቆላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም ሀገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በጎቹ በተቈጣጣሪያቸው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች በቈላውም ባሉ ከተሞች በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች መንጎቹ በተቈጣጣሪው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
የሚቃጠለው መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕትን፥ የእህሉንም ቁርባን ዕጣኑንም፥ የምስጋናውንም መሥዋዕት ይዘው ከይሁዳ ከተሞች ከኢየሩሳሌምም ዙሪያ፥ ከብንያምም አገር፥ ከቈላውም ከደጋውም ከደቡብም ወደ ጌታ ቤት ይመጣሉ።
ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ ላይ ሆነው እልል ይላሉ፤ ስለ ጌታም በጎነቱ፥ ስለ እህሉና ስለ ወይን ጠጁ፥ ስለ ዘይቱም፥ ስለ በጎቹና ስለ ከብቶቹ በሐሤት ይሞላሉ፤ ነፍሳቸውም ውኃ ጠጥታ እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም።
ምርኮኞቻቸውንም እመልሳለሁና በብንያም አገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች፥ በደጋውም ባሉ ከተሞች፥ በቈላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች ሰዎች እርሻውን በብር ይገዛሉ፥ ምስክሮችንም ጠርተው በውሉ ሰነድ ላይ ፈርመው ያትሙታል፥ ይላል ጌታ።”
ይህም የእስራኤል ልጆች የጦር ምርኮ የከነዓንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳል፥ በስፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ምርኮኞች የደቡብን ከተሞች ይወርሳሉ።