በዚህም ጉዳይ ከመከረበት በኋላ የሁለት ጥጆችን ምስል ከወርቅ አሠርቶ ለሕዝቡ “ከዚህ በፊት ታደርጉት በነበረው ዓይነት ለመስገድ እስከ ኢየሩሳሌም መሄድ ይበቃችኋል፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነሆ እነዚህ ናቸው!” አለ።
ኢሳይያስ 44:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጣዖትን የሠራ ወይስ ለምንም የማይረባን ምስልን የቀረጸ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለምንም የማይጠቅመውን አምላክ የሚቀርጽ፣ ጣዖትን የሚያበጅስ ማነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ምንም የማይጠቅም ጣዖትን ወይም ምስልን ይሠራል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጣዖታትን የሚሠሩ፥ የማይጠቅማቸውን ምስል የሚቀርጹና በእነርሱም የተሠሩ ሁሉ ይደርቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክን የሠራ ወይስ ለምንም የማይረባ ምስልን የቀረጸ ማን ነው? |
በዚህም ጉዳይ ከመከረበት በኋላ የሁለት ጥጆችን ምስል ከወርቅ አሠርቶ ለሕዝቡ “ከዚህ በፊት ታደርጉት በነበረው ዓይነት ለመስገድ እስከ ኢየሩሳሌም መሄድ ይበቃችኋል፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነሆ እነዚህ ናቸው!” አለ።
እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።
በዱባ እርሻ (የአትክልት ስፍራ) ውስጥ እንዳለ እንደ ወፍ ማስፈራርያ ዓምድ ናቸው፥ እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም ስለማይችሉ ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራት አይችሉምና፥ ደግሞም መልካም መሥራት በእነርሱ ውስጥ የለምና አትፍሩአቸው።”
አቤቱ! ኃይሌ፥ አምባዬ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ፥ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር የማይረባቸውንም ወርሰዋል፤
ሠሪው የቀረጸውና ቀልጦ የተሠራ ምስል የውሸት አስተማሪ ነውና፤ ዲዳ ጣዖትን በመሥራት ሠሪው በሠራው ይታመናልና፤ የተቀረጸ ምስል ምን ይጠቅማል?
ይህም ጳውሎስ ‘በእጅ የተሠሩቱ አማልክት አይደሉም፤’ ብሎ፥ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ክፍል በቀር በእስያ ሁሉ ብዙ ሕዝብን እንደ አስረዳና እንደ አሳተ አይታችኋል፤ ሰምታችሁማል።