አንቺ ጩኸትና ፍጅት የሞላብሽ ከተማ፥ የፈንጠዚያ ከተማ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉምን፥ በሰልፍስ የሞቱ አይደሉም?
ኢሳይያስ 10:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፤ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም። እጁም እንደ ተዘረጋ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእስረኞች ጋራ ከመርበትበት፣ ከታረዱትም ጋራ ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመማረክና ከመገደል እንዴት ታመልጣላችሁ? ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ ገና አልበረደም፤ ስለዚህ እናንተን ለመቅጣት እጁ እንደ ተሰነዘረ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሐሣር እንዳትወድቁ፥ ክብራችሁን ወዴት ትተዉታላችሁ? በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስረኞች በታች ያጐነብሳሉ፥ ከተገደሉትም በታች ይወድቃሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች። |
አንቺ ጩኸትና ፍጅት የሞላብሽ ከተማ፥ የፈንጠዚያ ከተማ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉምን፥ በሰልፍስ የሞቱ አይደሉም?
የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነዶአል፤ እጁን አንሥቶ መቶአቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ቁጣው ገና አልተመለሰም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
ሶርያውያን ከምሥራቅ፤ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤ አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫጭቋታል። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁ እንደ ተዘረጋ ነው።
ስለዚህ ጌታ በጎበዛዝት ደስ አይሰኝም፤ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረበትና ክፉ አድራጊ ነው፤ የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾህንና ኩርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነዳል፤ ጢሱም ተትጐልጉሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።
ምናሴ ኤፍሬምን፤ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤ በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
እነርሱም፦ ‘ወዴት እንውጣ?’ ቢሉህ፥ አንተ፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰይፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለምርኮም የሆነ ወደ ምርኮ’ ትላቸዋለህ።
እናንተንም የሚወጉዋችሁን የከለዳውያንን ሠራዊት ሁሉ ድል ብታደርጉ እንኳ ከእነርሱም መካከል የቆሰሉ ሰዎች ብቻ ቢቀሩ፥ እነርሱም ሁሉ ከየድንኳኖቻቸው ይነሣሉ ይህችንም ከተማ በእሳት ያቃጥላታል።’ ”