ዲሶን፥ ኤጽር፥ ዲሳን፥ እነዚህ በኤዶም ምድር የሖሪው የሴይር ልጆች አለቆች ናቸው።
ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
ዲሾን፥ ኤጼርና፥ ዲሻን ናቸው።
ዲሶን፥ ኤሶር፥ ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም ምድር የሖሪያዊው የሴይር ልጆች መሳፍንት ናቸው።
ፅብዖም፥ ዓን፥ ዲሶን፥ ኤጽር፥ ዲሳን እንዚህ በኤዶም ምድር የሖሪው የሴይር ልጆች አለቆች ናቸው።
በዚያች አገር የተቀመጡ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ሎጣን፥ ሾባል፥ ፅብዖን፥ ዓናና፥
የሎጣን ልጆችም ሖሪ፥ ሄማን ናቸው፥ የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ናት።
የኤጽር ልጆች ቢልሃን፥ ዛዕዋንና፥ ዓቃን ናቸው።
የዲሾን አለቃ፥ ኤጽር አለቃ፥ ዲሻን አለቃ፥ በሴይር ምድር አለቆች የሆኑ የሖሪ አለቆቹ እነዚህ ናቸው።
የሴይርም ልጆች፤ ሎጣን፥ ሦባል፥ ጽብዖን፥ ዓና፥ ዲሶን፥ ኤጽር፥ ዲሳን ናቸው።