ዘፍጥረት 34:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀብታቸውን ሁሉ ሕፃናቶቻቸውንና ሴቶቻቸውንም ሁሉ ማረኩ፥ በቤት ያለውንም ሁሉ ዘረፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሀብታቸውን ሁሉ ዘርፈው ሴቶቻቸውንና ሕፃኖቻቸውን ሁሉ ማርከው በየቤቱ ያገኙትን ሁሉ ይዘው ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቶችንና ሕፃናትን ማረኩ፤ በየቤቱ ያገኙትን ሀብት ሁሉ ዘረፉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎሌዎቻቸውንና ሚስቶቻቸውን፥ የቤታቸውንም ቈሳቍስ ሁሉ ማረኩ፤ በቤትና በከተማ ያለውንም ሁሉ ዘረፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሀብታቸውን ሁሉ ሕፃናቶቻቸውንና ሴቶቻቸውንም፥ ሁሉ ማረኩ በቤት ያለውንም ሁሉ ዘረፉ። |
ያዕቆብም ሌዊንና ስሞዖንን እንዲህ አለ፦ “በዚች አገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ሰዎች የተጠላሁ ታደርጉኝ ዘንድ እኔን አስጨነቃችሁኝ፥ እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፥ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይመቱኛል፥ እኔም ከወገኔ ጋር እጠፋለሁ።”