La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 31:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለምን በስውር ሸሸህ፥ እኔንም አታለልከኝ፥ በደስታና በዘፈንም በከበሮና በበገና እንድሰድድህ ለምን አልነገርኸኝም?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለመሆኑ ለምን ተደብቀህ ሄድህ? ለምንስ አታለልኸኝ? ብትነግረኝ ኖሮ፣ በደስታና በዘፈን በከበሮና በበገና አልሸኝህም ነበር?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳትነግረኝ ተሰውረህ በመሄድ ለምን አታለልከኝ? ነግረኸኝ ቢሆን ኖሮ በከበሮና በመሰንቆ እየተዘፈነ በደስታ በሸኘሁህ ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብት​ነ​ግ​ረኝ ኑሮ በደ​ስ​ታና በሐ​ሴት፥ በዘ​ፈን፥ በከ​በ​ሮና በበ​ገና በሸ​ኘ​ሁህ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለምን በስውር ሸሸህ? ከእኔም ከድተህ ስለምን ኮበለልህ? በደስታና በዘፈም በከበሮና በበገና እንድሰድድህ ለምን አልነገርኸኝም?

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 31:27
11 Referencias Cruzadas  

ላባም ያዕቆብን አለው፥ “የፈጸምከው ምንድነው? እኔን አታልልከኝ፥ ልጆቼንስ እንደ ሰይፍ ምርኮኛ ለምን ወሰድካቸው?


ያዕቆብም መለሰ ላባንም እንዲህ አለው፥ “ልጆችህን በጉልበት ከእኔ የምትቀማኝ ስለ መሰለኝና ስለ ፈራሁ ይህን አደረግሁ።


የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ፥ እርሱም በገናንና ዋሽንትን ለሚይዙ አባት ነበረ።


የአሮን እኅት ነቢይቱ ማሪያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች፤ ሴቶችም ሁሉ ከበሮ በመያዝና በጭፈራ በኋላዋ ወጡ።


በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፤ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለጌታ ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።


ጌዴዎን ከአገልጋዮቹ ዐሥር ሰዎች ወስዶ ጌታ እንዳዘዘው አደረገ፤ ቤተሰቡንና የከተማውን ሰው ስለ ፈራ ይህን ያደረገው ቀን ሳይሆን ሌሊት ነበር።