La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕዝራ 8:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ካህናቱና ሌዋውያኑም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አምላካችን ቤት ለመውሰድ ብሩንና ወርቁን ዕቃዎቹንም በሚዛን ተቀበሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ካህናቱና ሌዋውያኑ ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ አምላካችን ቤት እንዲሄድ የተመዘነውን ብር፣ ወርቅና ንዋያተ ቅድሳት ተረከቡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም ካህናቱና ሌዋውያኑ ብሩንና ወርቁን፥ ጠቅላላውንም ንዋያተ ቅድሳት ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ለመውሰድ ኀላፊነትን ተረከቡ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም በሚ​ዛን ተቀ​በሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ካህናቱና ሌዋውያኑም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አምላካችን ቤት ይወስዱት ዘንድ ብሩንና ወርቁን፥ ዕቃዎቹንም በሚዛን ተቀበሉ።

Ver Capítulo



ዕዝራ 8:30
6 Referencias Cruzadas  

ቁጥራቸውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወርቅ ሰሐኖች፥ አንድ ሺህ የብር ሰሐኖች፥ ሀያ ዘጠኝ ቢላዋዎች፥


ንጉሡንም፦ “የአምላካችን እጅ በሚፈልጉት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፥ ኃይሉና ቁጣውም እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተናግረን ነበርና በመንገድ ካለው ጠላት እንዲያድኑን ወታደሮችና ፈረሰኞች ከንጉሡ ለመጠየቅ አፍሬ ነበር።


በአራተኛውም ቀን ብሩ፥ ወርቁና ዕቃዎቹም በአምላካችን ቤት በካህኑ በኡሪያ ልጅ በምሬሞት እጅ ተመዘነ፤ ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ። ከእነርሱም ጋር ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባድና የቢኑይ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ።


ስለ ጌታ አምላካችን ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ።


የመቅደሴንም ስፍራ ለማስጌጥ የሊባኖስ ክብር፥ ጥዱና አስታው፥ ባርሰነቱም ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ።