ዕዝራ 8:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 በካህናት አለቆች፥ በሌዋውያን በእስራኤል አባቶች አለቆች ፊት በኢየሩሳሌም በጌታ ቤት ክፍሎች ውስጥ እስክትመዝኑ ድረስ በጥንቃቄ ጠብቋቸው።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ኢየሩሳሌም በሚገኘው በእግዚአብሔር ቤት ክፍሎች ውስጥ በዋና ዋናዎቹ ካህናት፣ በሌዋውያኑና በየቤተ ሰቡ የእስራኤል አለቆች ፊት እስክትመዝኗቸው ድረስ በጥንቃቄ ጠብቋቸው።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ወደ ቤተ መቅደስ መግባት እስኪችሉ ድረስ በጥንቃቄ ጠብቁአቸው፤ እዚያም ለካህናቱ በተመደበው ክፍል ውስጥ እነዚህን ሁሉ ንዋያተ ቅድሳት መዝናችሁ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ መሪዎች እንዲሁም በኢየሩሳሌም ለሚገኙት የሕዝቡ መሪዎች አስረክቡአቸው።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 በካህናትና በሌዋውያን አለቆች፥ በእስራኤልም አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ቤት ጓዳዎች ውስጥ እስክትመዝኑ ድረስ ተግታችሁ ጠብቁ” አልኋቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 በካህናትና በሌዋውያን አለቆች፥ በእስራኤልም አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ቤት ጓዳዎች ውስጥ እስክትመዝኑ ድረስ ተግታችሁ ጠብቁ” አልኋቸው። Ver Capítulo |