ለጌታም ቤት አገልግሎት የመገናኛውን ድንኳን ሥርዓት የመቅደሱንም ሥርዓት የወንድሞቻቸውንም የአሮንን ልጆች ሥርዓት በመጠበቅ ያገለግሉ ነበረ።”
ሕዝቅኤል 44:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅደሴ ውስጥ ሥርዓቴን ጠባቂዎች ለራሳችሁ አስቀመጣችሁ እንጂ የተቀደሰውን ነገሬን ሥርዓት አልጠበቃችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ራሳችሁ ማድረግ የሚገባችሁን ቅዱሳት ሥርዐቶቼን በመፈጸም ፈንታ ባዕዳንን በኀላፊነት በመቅደሴ አስቀመጣችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተቀደሰ ቊርባኔንም በኀላፊነት አልጠበቃችሁም፤ እንዲያውም በተሰጣችሁ የኀላፊነት ቦታ ላይ ባዕዳንን መደባችሁበት።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመቅደሴን ሥርዐት አልጠበቃችሁም፤ ነገር ግን የመቅደሴን ሥርዐት የሚጠብቁ ሌሎችን ለራሳችሁ ሾማችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቅደሴ ውስጥ ለራሳችሁ ሥርዓቴን ጠባቂዎች አደረጋችሁ እንጂ የተቀደሰውን ነገሬን ሥርዓት አልጠበቃችሁም። |
ለጌታም ቤት አገልግሎት የመገናኛውን ድንኳን ሥርዓት የመቅደሱንም ሥርዓት የወንድሞቻቸውንም የአሮንን ልጆች ሥርዓት በመጠበቅ ያገለግሉ ነበረ።”
አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ለመሠዊያው የሚደረገውን ነገር ሁሉ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የሚሆነውን እንድታደርጉ የክህነታችሁን ግዴታዎች በትጋት ፈጽሙ፥ አገልግሉም፤ ክህነታችሁን እንደ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁ፤ ሌላም ሰው ቢቀርብ ይገደል።”
ወንድሞቻቸው የተሰጣቸውን ግዴታ እንዲወጡ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይርዱአቸው እንጂ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩ። በየአገልግሎታቸው በመደልደል በሌዋውያን ላይ እንዲሁ ታደርጋለህ።”