La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 41:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የመግቢያው ወርድ ዐሥር ክንድ ነበረ፥ የመግቢያው መቃኖች በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያ ወገን ደግሞ አምስት ክንድ ነበሩ፤ ርዝመቱን አርባ ክንድ ወርዱን ደግሞ ሀያ ክንድ አድርጎ ለካ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የመግቢያውም በር ወርድ ዐሥር ክንድ ሲሆን፣ በግራና በቀኝ በኩል ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች ወርድ ዐምስት ክንድ ነበር። ደግሞም የውስጡን መቅደስ ለካ፤ ርዝመቱ አርባ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወርዱም ዐሥር ክንድ ሆነ፤ በግራና ቀኝ የሚገኙትም ግንቦች የእያንዳንዱ ውፍረት አምስት ክንድ ነበር፤ የተቀደሰው ስፍራ ሲለካ ርዝመቱ አርባ ክንድ፥ ወርዱም ኻያ ክንድ ሆነ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም ወርድ ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም መቃ​ኖች በዚህ ወገን አም​ስት ክንድ፥ በዚ​ያም ወገን አም​ስት ክንድ ነበሩ፤ ርዝ​መ​ቱ​ንም አርባ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም ሃያ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የመግቢያውም ወርድ አሥር ክንድ ነበረ፥ የመግቢያውም መቃኖች በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያም ወገን አምስት ክንድ ነበሩ፥ ርዝመቱንም አርባ ክንድ ወርዱንም ሀያ ክንድ አድርጎ ለካ።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 41:2
11 Referencias Cruzadas  

ከቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት የሚገኘውም የተቀደሰ ክፍል ርዝመቱ ዐሥራ ስምንት ሜትር ነበር።


ለጌታ የሠራው ቤተ መቅደስ ርዝመቱ ኻያ ሰባት ሜትር፥ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፥ ቁመቱ ዐሥራ ሦስት ሜትር ተኩል ነበር።


ደግሞም ዋና የመግቢያ ደጆችን ዘጉ፥ መብራቶቹንም አጥፍተዋል፥ በመቅደሱም ውስጥ ለእስራኤል አምላክ አላጠኑም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አላቀረቡም።


ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት የጣለው መሠረት ይህ ነው፤ ርዝመቱም በዱሮው መለክያ መሠረት ስልሳ ክንድ፥ ወርዱም ሀያ ክንድ ነበረ።


ቤቱንም ሰረገሎቹንም መድረኮቹንም ግንቦቹንም ደጆቹንም በወርቅ ለበጠ በግንቦቹም ላይ ኪሩቤልን ቀረጸ።


ለድንኳኑም ደጃፍ ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም በጥልፍ አሠራር የተሠራ መጋረጃ አድርግለት።


ለድንኳኑም ደጃፍ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተጠለፈ መጋረጃ አደረገ፤


ወደ ቤቱ መግቢያ መለሰኝ፤ እነሆ ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፥ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና፤ ውኃውም ከቤቱ በስተ ቀኝ በኩል በታች በመሠዊያው በደቡብ በኩል ይወርድ ነበር።


ኢየሱስም ደግሞ አላቸው “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እኔ የበጎች በር ነኝ።


በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፤ ይገባልም፤ ይወጣልም፤ መሰማሪያም ያገኛል።