ወደ ደቡብ መራኝ፥ እነሆ ወደ ደቡብ የሚመለከት በር ነበረ፤ የግንቡን አዕማድና መተላለፊያዎቹንም እንደዚያው መጠን አድርጎ ለካ። ከሌሎቹም ጋር እኩል መጠን ነበራቸው።
ሕዝቅኤል 40:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውጭው አደባባይ ያለ ወደ ሰሜን የሚመለከተውን በር ርዝመትና ወርዱን ለካ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በሰሜን ትይዩ ያለውን፣ ወደ ውጩ አደባባይ የሚያመራውን በር ርዝመትና ወርድ ለካ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያ ሰው በሰሜን በኩል ወደ ውጪው አደባባይ ትይዩ ያለውን የቅጽር በር ለካ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሰሜንም መራኝ፤ እነሆም በውጭው አደባባይ ያለ ወደ ሰሜን የሚመለከት በር ነበረ፤ ርዝመቱንና ወርዱንም ለካ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሰሜንም መራኝ፥ እነሆም፥ በውጭው አደባባይ ያለ ወደ ሰሜን የሚመለከት በር ነበረ፥ ርዝመቱንና ወርዱንም ለካ። |
ወደ ደቡብ መራኝ፥ እነሆ ወደ ደቡብ የሚመለከት በር ነበረ፤ የግንቡን አዕማድና መተላለፊያዎቹንም እንደዚያው መጠን አድርጎ ለካ። ከሌሎቹም ጋር እኩል መጠን ነበራቸው።
ፊቱ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በር መጣ፥ በደረጃዎቹም ወጥቶ በበሩ በኩል ያለውን የቤቱን መግቢያ ወለል ወርዱን ለካ አንድ ዘንግ ነበር፥ የሌላኛውም የቤቱ መግቢያ ወለል ወርድ አንድ ዘንግ ነበር።
በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ውጪው አደባባይ አወጣኝ፥ በተለየው ስፍራ ፊት ለፊት፥ በሰሜን በኩል ባለው ህንጻ ፊት ለፊት ወዳለው ክፍል አገባኝ።
ከመቅደሱ ውጭ ያለውን አደባባይ ግን ተወው፤ አትለካውም፥ ምክንያቱም ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና፤ እነርሱም ለአርባ ሁለት ወር ያህል የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።