La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 4:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንተም በግራ ጐንህ ተኛ፥ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት አኑርባት፥ በምትተኛበትም ቀኖች ቍጥር ኃጢአታቸውን ትሸከማለህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“አንተ በግራ ጐንህ ተኛ፤ የእስራኤልም ቤት ኀጢአት በአንተ ላይ ይሁን፤ በዚህ ጐንህ በተኛህበት ቀን ቍጥር ኀጢአታቸውን ትሸከማለህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እንግዲህ በግራ ጐንህ ተኝተህ የእስራኤላውያንን ኃጢአት ተሸከም፤ በጐንህ በምትተኛባቸው ቀኖች ቊጥር የእነርሱን ኃጢአት ትሸከማለህ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“አን​ተም በግራ ጎንህ ተኛ፤ በም​ት​ተ​ኛ​በ​ትም ቀን ቍጥር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ኀጢ​አት አኑ​ር​ባት፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ትሸ​ከ​ማ​ለህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንተም በግራ ጐድንህ ተኛ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት አኑርባት በምትተኛበትም ቀን ቍጥር ኃጢአታቸውን ትሸከማለህ።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 4:4
11 Referencias Cruzadas  

እኔም የኃጢአታቸውን ዓመታት ለአንተ የቀኖች ቍጥር እንዲሆንልህ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ሰጥቼሃለሁ፥ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት ትሸከማለህ።


እነሆም ገመድ አደርግብሃለሁ፥ የምትከበብበትንም ቀኖች እስክትፈጽም ድረስ ከአንዱ ጎንህ ወደ ሌላው ጎንህ አትገላበጥም።


“እጅግ የተቀደሰ ነውና፥ የሕዝቡንም ኃጢአት እንድትሸከሙ፥ በጌታም ፊት እንድታስተሰርዩላቸው ለእናንተ ሰጥቶአልና ለምን የኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን በቅዱሱ ስፍራ አልበላችሁም?


ፍየሉም በደላቸውን ሁሉ በረሀ ወደ ሆነ ስፍራ ይሸከማል፤ ፍየሉንም በምድረ በዳ ውስጥ እንዲሄድ ይለቅቀዋል።


ምድሪቱን በሰላለችሁባት ቀን ቍጥር፥ አርባ ቀን፥ እያንዳንዱም ቀን እንደ አንድ ዓመት ሆኖ፥ በደላችሁን አርባ ዓመት ትሸከማላችሁ፥ መከፋቴንም ታውቃላችሁ።’


ጌታም አሮንን እንዲህ አለው፦ “አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህና የአባቶችህ ቤት ከመቅደሱ ጋር በተገናኘ የሚፈጸምን በደል ትሸከማላችሁ፤ አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ከክህነታችሁ ጋር በተገናኘ የሚፈጸምን በደል ትሸከማላችሁ።


ይህም በነቢዩ ኢሳይያስ “እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸከመ፤” የተባለው እንዲፈጸም ነው።


እንዲሁም ክርስቶስ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ተሰውቷል። ለሁለተኛ ጊዜ ሲታይ ሊያድናቸው ለሚጠባበቁት ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን መዳንን ለማምጣት ነው።


ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቁስል እናንተ ተፈውሳችኋል።