ዘፀአት 39:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለት የወርቅ ቀለበቶችንም ሠሩ፥ እነርሱንም በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው በደረቱ ኪስ በሁለት ጫፎቹ ላይ አደረጉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ከኤፉዱ ቀጥሎ ካሉት ከሌሎቹ ሁለት የደረት ኪስ ጐኖች ጋራ ከውስጠኛው ጠርዝ ላይ አያያዟቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተጨማሪም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተው በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው የደረት ኪስ ሁለት የውስጥ ጫፎች ላይ አደረጉአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱንም የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፤ እነርሱንም ከልብሰ መትከፉ ፊት ለፊት ባለው በልብሰ እንግድዓው በሁለቱ ጫፎች ላይ አደረጓቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱንም የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፥ እነርሱንም በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው በደረቱ ኪስ በሁለት ጫፎቹ ላይ አደረጉአቸው። |
ደግሞም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፥ በኤፉዱም ፊት፥ ከትከሻዎቹ በታች፥ በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቋድ በላይ፥ በመያዣው አጠገብ አደረጉአቸው።