ዘፀአት 34:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛሬ የማዝዝህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ እኔ አሞራዊውን፥ ከነዓናዊውን፥ ኬጢያዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን በፊትህ አወጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛሬ የማዝዝህን ፈጽም፤ አሞራውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ኬጢያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያውያንንና ኢያቡሳውያንን በፊትህ አስወጣቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዛሬ ለእናንተ የምሰጠውን ሕግ ጠብቁ፤ እኔም አሞራውያንን፥ ከነዓናውያንን፥ ሒታውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ሒዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ አባርራለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ ቀን የማዝዝህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ፥ እኔ አሞሬዎናዊውን፥ ከነዓናዊውንም፥ ኬጤዎናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ከፊትህ አወጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህ ቀን የማዝዝህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ እኔ አሞራዊውን ከነዓናዊውንም ኬጢያዊውንም ፌርዛዊውንም ኤዊያዊውንም ኢያቡሳዊውንም በፊትህ አወጣለሁ። |
ከግብጽም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ።’
ከግብፃውያን እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወደ መልካምና ሰፊ አገር፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ኤሞራውያን፥ ፌርዛውያን፥ ሒዊያውያን፥ የቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”
በአምላክህ በጌታ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፥ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ለዘለዓለም መልካም እንዲሆንላችሁ፥ እኔ የምሰጥህን እነዚህን ደንቦች ሁሉ በጥንቃቄ ፈጽማቸው።”
“ለጌታ እግዚአብሔር ፍጹም ብትታዘዝና እኔ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዙን ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቅ፥ ጌታ እግዚአብሔር በምድር ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”
እንግዲህ፥ እስራኤል ሆይ፥ ስማ! መልካም እንዲሆንልህ፥ የአባቶችህም አምላክ ጌታ እንደ ተናገረ፥ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር፥ እጅግ እንድትበዛ በጥንቃቄ ጠብቅ።
ዓይንህ ያየችውን ታላቅን መቅሠፍት፥ ምልክትንም፥ ተአምራትንም፥ ጌታ አምላክህ ሲያስወጣህ የጸናችውን እጅ፥ የተዘረጋውንም ክንድ፥ እንደዚሁ ሁሉ ጌታ አምላክህ አንተ በምትፈራቸው በሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደርጋል።
ጌታ አምላካቸሁም እርሱ ከፊታችሁ በብርቱ ገፍቶ ያስወጣቸዋል፥ ከፊታችሁም ያሳድዳቸዋል፤ ጌታ አምላካችሁ እንደ ተናገራችሁም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ።