ዘፀአት 29:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉንም በአሮን እጆችና በልጆቹ እጆች ላይ ታኖረዋለህ፤ ለሚወዘወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ትወዘውዘዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህን ሁሉ በአሮንና በወንዶች ልጆቹ እጆች ላይ በማኖር እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ወዝውዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሁሉ ምግብ በአሮንና በልጆቹ እጅ ላይ አኑር፤ እርሱንም ወዝውዘው ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉንም በአሮን እጆችና በልጆቹ እጆች ታኖረዋለህ፤ ለሚለይ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትለየዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉንም በአሮን እጆችና በልጆቹ እጆች ታኖረዋለህ፤ ለሚወዘወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትወዘውዘዋለህ። |
ከእጃቸውም ትቀበለዋለህ፥ በጌታ ፊት መልካም መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ታቃጥለዋለህ፤ ይህም ለጌታ የእሳት ቁርባን ነው።
ነገር ግን የሚወዘወዘውን ፍርምባ፥ የሚነሣውንም ወርች አንተ፥ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶች ልጆችህና ሴቶች ልጆችህም በንጹሕ ስፍራ ትበላላችሁ፤ እነዚህ ከእስራኤል ልጆች ከሰላም መሥዋዕት ለአንተና ለልጆችህ ድርሻ እንዲሆኑ የተሰጡ ናቸውና።
የእርሱ እጆች ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያመጣሉ፤ እርሱም ፍርምባው በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን እንዲወዘወዝ ፍርምባውን ከስቡ ጋር ያመጣዋል።