ዘፀአት 29:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ፥ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱን ኩላሊቶችና በላያቸው ያለውን ስብ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በሆድ ዕቃዎች ያለውን ስብ ሁሉ፣ የጕበቱን መሸፈኛና ሁለቱንም ኵላሊቶች በዙሪያቸው ካለው ስብ ጋራ ወስደህ በመሠዊያው ላይ አቃጥላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሞራ እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን የሚሸፍነውን ሞራ ሁለቱን ኲላሊቶቹንና እነርሱን የሚሸፍነውን ሞራ ወስደህ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በላያቸውም ያለውን ስብ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ታስቀምጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ በጉልበቱም ላይ ያለውን መረብ ሁለቱንም ኵላሊቶች በላያቸውም ያለውን ስብ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ። |
ለክህነት ሥርዓት የቀረበ አውራ በግ ነውና የበጉን ስብ፥ ላቱን፥ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱን ኩላሊቶቹ፥ በላያቸውም ያለውን ስብና የቀኙን ወርች ትወስዳለህ።
ከእጃቸውም ትቀበለዋለህ፥ በጌታ ፊት መልካም መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ታቃጥለዋለህ፤ ይህም ለጌታ የእሳት ቁርባን ነው።
“የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምኔ ነው?” ይላል ጌታ። የሚቃጠለውን የአውራ በግና የሰቡ እንስሳትን ስብ ጠግቤአለሁ፤ በበሬ፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም ደስ አልሰኝም።
ጌታ መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና፥ የጌታ ሰይፍ በደም ትርሳለች፤ ስብ ትጠግባለች፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ኩላሊት ስብ ትወፍራለች።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል፤ ካህኑም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ በእሳትም የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ፥ በጌታ ዘንድ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ሁሉንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
ከአንድነት መሥዋዕት ላይ እንደተወሰደው ስብ እንዲሁ የእርሷን ስብ ሁሉ ይወስዳል፤ ካህኑም ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፤ ካህኑም ስለ እርሱ ያስተሰርያል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው ጠቦት ላይ ስቡ እንደሚወሰድ እንዲሁ የእርሷን ስብ ሁሉ ይወስዳል፤ ካህኑም ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ጋር በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይንደድበት፥ አይጥፋም፤ ካህኑም ማለዳ ማለዳ እንጨት ያቃጥለበታል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በዚያ ላይ ይረበርባል፤ እንዲሁም የአንድነትን መሥዋዕት ስብ በዚያ ላይ ያቃጥላል።
በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኩላሊቶች ከስባቸው ጋር ወሰደ፤ ሙሴም በመሠዊያው ላይ አቃጠለው።
ከዚያም በኋላ ስቡንና ላቱን፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኩላሊቶች ስባቸውንም፥ ቀኝ ወርቹንም ወሰደ፤
ነገር ግን የላም በኵራት ወይም የበግ በኵራት ወይም የፍየል በኵራት አትዋጅም፤ የተቀደሱ ናቸው፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ እርጨው፥ ስባቸውንም ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርገህ አቃጥለው።
ሰውየውም፦ “አስቀድሞ ስቡን ያቃጥሉት፥ ከዚያም በኋላ ሰውነትህ ደስ የሚያሰኛትን ያህል ትወስዳለህ” ቢለው፥ እርሱ፦ “አይሆንም፥ አሁን ልትሰጠኝ ይገባል፤ ካልሆነ ግን በግድ እወስዳለሁ!” ይለው ነበር።