በባልንጀራው ንብረት ላይ እጁን እንዳልዘረጋ የጌታ መሐላ በሁለታቸው መካከል ይሁን፤ የከብቱም ባለቤት መሐላውን ይቀበል፥ እርሱም ምንም አይክፈል።
ዘፀአት 22:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱ ከተሰረቀ ግን ለባለቤቱ ይክፈል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሁለቱ መካከል ያለው አለመግባባት መፍትሒ የሚያገኘው፣ ጎረቤቱ የሌላውን ሰው ንብረት እንዳልወሰደ በእግዚአብሔር ፊት በመማል ነው። ባለቤቱም ይህን መቀበል አለበት፤ የካሳም ክፍያ አይጠየቅም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያ ሰው የእግዚአብሔር አገልጋዮች ወደሆኑት ዳኞች ዘንድ ይሂድ፤ የሰውዬውን እንስሳ አለመስረቁንም በመሐላ ያረጋግጥ፤ እንስሳው ያልተሰረቀ ከሆነ የእንስሳው ባለቤት ካሳ አይጠይቅ፤ እንስሳው የጠፋበትም ሰው ካሳ አይክፈል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባልንጀራው ከብት ላይ እጁን እንዳልዘረጋ የእግዚአብሔር መሐላ በሁለታቸው መካከል ይሁን፤ የከብቱም ባለቤት ይህን ከተቀበለ፥ እርሱ ምንም አይክፈል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባልንጀራው ከብት ላይ እጁን እንዳልዘረጋ የእግዚአብሔር መሐላ በሁለታቸው መካከል ይሁን፤ የከብቱም ባለቤት መሐላውን ይቀበል፥ እርሱም ምንም አይክፈል። |
በባልንጀራው ንብረት ላይ እጁን እንዳልዘረጋ የጌታ መሐላ በሁለታቸው መካከል ይሁን፤ የከብቱም ባለቤት መሐላውን ይቀበል፥ እርሱም ምንም አይክፈል።
ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለ ሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ይህ የእኔ ነው ቢል ክርክራቸው ወደ እግዚአብሔር ይምጣ፤ እግዚአብሔርም የፈረደበት እርሱ ለባልንጀራው እጥፍ አድርጎ ይክፈል።