ነገር ግን በሬው አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ለባለቤቱ አስጠንቅቀውት ባይጠብቀውና ወንድን ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል።
ዘፀአት 21:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሬው አስቀድሞ ተዋጊ መሆኑ ቢታወቅ፥ ባለቤቱም ባይጠብቀው፥ በሬውን በበሬው ፈንታ ይስጥ፥ የሞተውም ለእርሱ ይሁነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም በሬው የመዋጋት ዐመል ያለው መሆኑ ከታወቀ፣ ባለቤቱም በረት ሳይዘጋበት ቢቀር፣ ባለቤቱ በሬውን በበሬው ፈንታ ይክፈል፤ የሞተውም እንስሳ ለርሱ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በሬው ተዋጊ መሆኑ ታውቆ ሳለ ባለቤቱ በበረት ውስጥ ሳይዘው ቀርቶ ከሆነ፥ በሬው ለሞተበት ሰው አንድ በሕይወት ያለ በሬ ካሣ ይክፈል፤ የሞተውንም በሬ ለራሱ ያስቀር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሬውም ትናንትና ከትናንት ወዲያ ተዋጊ መሆኑ ቢታወቅ ለባለቤቱም ቢመሰክሩለት፥ ባለቤቱም ባያስወግደው በሬውን በበሬው ፋንታ ይስጥ፤ የሞተውም ለእርሱ ይሁነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሬውም አስቀድሞ ተዋጊ መሆኑ ቢታወቅ፥ ባለቤቱም ባይጠብቀው፥ በሬውን በበሬው ፈንታ ይስጥ፥ የሞተውም ለእርሱ ይሁነው። |
ነገር ግን በሬው አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ለባለቤቱ አስጠንቅቀውት ባይጠብቀውና ወንድን ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል።
የአንድ ሰው በሬ የሌላውን በሬ ቢወጋ፥ ቢሞትም፥ በሕይወት ያለውን በሬ ይሽጡ፥ ዋጋውንም እኩል ይካፈሉት፤ የሞተውንም ደግሞ እኩል ይካፈሉ።