La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 17:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴ፥ አሮንና ሑር ወደ ኮረብታው ጫፍ ወጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ኢያሱ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ከአማሌቃውያን ጋራ ተዋጋ፤ ሙሴ፣ አሮንና ሖርም ወደ ኰረብታው ጫፍ ወጡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢያሱም የሙሴን ትእዛዝ በመፈጸም ዐማሌቃውያንን ለመውጋት ወጣ፤ ሙሴ፥ አሮንና ሑር ወደ ኮረብታው ጫፍ ወጡ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያ​ሱም ሙሴ እንደ አለው አደ​ረገ፤ ወጥ​ቶም ከዐ​ማ​ሌቅ ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮን፥ ሖርም ወደ ኮረ​ብ​ታው ራስ ወጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮንም ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 17:10
9 Referencias Cruzadas  

ዓዙባም ሞተች፥ ካሌብም ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሆርን ወለደችለት።


እንዲህም ሆነ ሙሴ እጁን ባነሣ ጊዜ እስራኤል ይበረታ ነበር፤ እጁንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ይበረታ ነበር።


የሙሴ እጆች ግን ዝለው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሑርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ያዙ፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ቀጥ አሉ።


ሽማግሌዎቹንም፦ “ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ በዚህ ቆዩን፤ አሮንና ሑርም እነሆ ከእናንተ ጋር ናቸው፥ ባለ ጉዳይም ቢኖር ወደ እነርሱ ይምጣ” አላቸው።


“እይ! ከይሁዳ ነገድ የሆነውን የሑር ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ ጠርቼዋለሁ።


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው፤ እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።


እናቱም ለአገልጋዮቹ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ፤” አለቻቸው።


ጌታም ባርያውን ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ሙሴ ኢያሱን አዝዞት ነበር፥ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ፤ ጌታ ሙሴን ካዘዘው ሁሉ ምንም አላስቀረም።