La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 10:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴንና አሮንን ወደ ፈርዖን አመጡአቸው፦ “ሂዱ፥ ጌታ አምላካችሁን አገልግሉ፥ ነገር ግን የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አላቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን እንዲመጡ ተደረገ፤ “ሂዱ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፤ ነገር ግን መሄድ የሚገባቸው የትኞቹ ናቸው?” አለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ሙሴና አሮን ተጠርተው ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ንጉሡም “ሄዳችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁን ማገልገል ትችላላችሁ፤ ነገር ግን መሄድ የሚገባቸው የትኞቹ ናቸው?” አላቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ወደ ፈር​ዖን ጠሩ​አ​ቸው፤ ፈር​ዖ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሂዱ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ፤ ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ሄ​ዱት እነ​ማን ናቸው?”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን መልሶ አስመጣቸው፤ ሂዱ፤ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ነገር ግን የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አላቸው።

Ver Capítulo



ዘፀአት 10:8
6 Referencias Cruzadas  

ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠራና እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ አምላካችሁንና እናንተን በደልሁ፤


ፈርዖንም ሙሴን ጠርቶ፦ “ሂዱ፥ ጌታን አገልግሉ፤ ነገር ግን በጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ተዉ፤ ልጆቻችሁም ከእናንተ ጋር ይሂዱ” አለው።


ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ፥ ከሕዝቤ መካከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እንዳላችሁትም ጌታን አገልግሉ፤


ሙሴም፦ “እነሆ እኔ ከአንተ ዘንድ እወጣለሁ፥ የዝንቡም መንጋ ከፈርዖን፥ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ነገ እንዲሄዱ ወደ ጌታ እጸልያለሁ፤ ነገር ግን ለጌታ ይሠዋ ዘንድ ሕዝቡን እንዳይለቅቅ ፈርዖን እንደገና አያታልለን” አለ።


ሙሴና አሮንም ከፈርዖን ዘንድ ወጡ። ሙሴም ከፈርዖን ጋር እንደተስማማው ስለ እንቁራሪቶቹ ወደ ጌታ ጮኸ።


የአምላክ ነጎድጓድ በረዶውም በዝቶአልና ወደ ጌታ ጸልዩ፤ እለቅቃችኋለሁ፥ ከዚህ በኋላ እዚህ አትቀመጡም።”