ዘዳግም 19:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላክህ ጌታ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር አማካይ ስፍራ፥ ሦስት ከተሞችን ለራስህ ትለያለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር አማካይ ስፍራ፣ ሦስት ከተሞችን ለራስህ ለይ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክህ እግዚአብሔር እንድትኖርባት የሚሰጥህን ምድር ለሦስት ትከፍልና በያንዳንዱ ክፍል አንዳንድ ከተማ የተለየ ታደርጋለህ፤ ነፍሰ ገዳይም ይሸሽባቸው ዘንድ ወደ እነዚያ የሚወስዱትን መንገዶች ታዘጋጃለህ፤ ከዚያ በኋላ አንድ ነፍሰ ገዳይ ሕይወቱን ለማትረፍ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ሸሽቶ ይሂድ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በምድርህ መካከል ሦስት ከተሞችን ለራስህ ትለያለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ በምድርህ መካከል ሦስት ከተሞችን ለራስህ ትለያለህ። |
በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ “ጌታ አምላካችሁ ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ የእናንተ ጦር ሰዎች ሁሉ ታጥቀው በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ።
ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።