ዘዳግም 16:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋውን ቀቅለህ አምላክህ ጌታ በሚመርጠው ቦታ ብላው፤ በማግስቱ ወደ ድንኳኖችህ ተመለስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥጋውንም ጠብሰህ አምላክህ እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ብላ፤ ሲነጋም ወደ ድንኳንህ ተመልሰህ ሂድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥጋውን ቀቅለህ እግዚአብሔር አምላክህ በሚመርጠው ቦታ ብላው፤ በማግስቱ ወደ ድንኳኖችህ ተመለስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ትጠብሰዋለህ፤ ታበስለዋለህም፤ ትበላውማለህ፤ በነጋውም ተመልሰህ ወደ ቤትህ ትሄዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ታበስለዋለህ፥ ትበላውማለህ፤ በነጋውም ተነሥተህ ወደ ድንኳንህ ትሄዳለህ። |
የፋሲካውንም መሥዋዕት እንደ ሥርዓቱ በእሳት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቁርባን በምንቸትና በሰታቴ በድስትም ቀቀሉ፥ ለሕዝቡም ሁሉ በፍጥነት አደረሱ።
ነገር ግን አምላክህ ጌታ ለስሙ መጠሪያ በመረጠው ስፍራ ብቻ፥ ፀሐይ ስትጠልቅ ከግብጽ በወጣህበት ቀን የወጣህበትን ሰዓት በመጠበቅ በዚያ ፋሲካን ሠዋ።