በዚያችም ሌሊት ጌታ ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፥ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፥ እባርክሃለሁ፥ ስለ ባርያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።”
ዘዳግም 13:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ከብርቱ ቁጣው እንዲመለስ እርም ነገሮች በእጅህ አይገኝ፤ እርሱ ምሕረቱን ያሳይሃል፤ ይራራልሃል፤ ለአባቶችህ በመሐላ ተስፋ በሰጠው መሠረት ቍጥር ህን ያበዛዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከብርቱ ቍጣው ይመለስ ዘንድ ዕርም ነገሮች በእጅህ አይገኙ፤ እርሱ ምሕረቱን ያሳይሃል፤ ይራራልሃል፤ ለአባቶችህ በመሐላ ተስፋ በሰጠው መሠረት ቍጥርህን ያበዛዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከአስፈሪ ቊጣው ተመልሶ ምሕረት ያደርግልህ ዘንድ እንዲወድም ከተወሰነው ሀብት አንዳችም ለራስህ አታስቀር፤ ይህን ብታደርግ ለአባቶችህ በመሐላ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ቊጥርህን ያበዛዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር የመቅሠፍቱ ቍጣ ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶችህም እንደ ማለላቸው ይምርህ ዘንድ፥ ይራራልህም ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆነው አንዳች ነገር በእጅህ አትንካ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ የሚያሰኘውን ታደርግ ዘንድ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ስትሰማ፥ የእግዚአብሔር መቅሠፍት ቁጣ ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶችህም እንደ ማለላቸው ይምርህ ዘንድ፥ ይራራልህም ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ፥ እርም ከሆነው አንዳች ነገር በእጅህ አይንጠልጠልብህ። |
በዚያችም ሌሊት ጌታ ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፥ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፥ እባርክሃለሁ፥ ስለ ባርያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።”
ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፥ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።
ግብፃውያን ‘በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከገጸ ምድር ሊያጠፋቸው ለክፋት ነው ያወጣቸው’ ለምን ይበሉ? ከቁጣህ መዓት ተመለስ፥ በሕዝብህ ጥፋት ላይ ራራ።
የሰላም ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደርጋለሁ፥ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆንላቸዋል፤ አጸናቸዋለሁ፥ አበዛቸዋለሁ፥ መቅደሴንም በመካከላቸው ለዘለዓለም አኖራለሁ።
እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥ በመካከልህም ቅዱሱ ነኝና የቁጣዬን መቅሠፍት አላደርግም፥ ኤፍሬምንም ዳግመኛ አላጠፋም፤ በመዓትም አልመጣም።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የጌታ የቁጣው ጽናት ከእስራኤል እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ በፀሐይ ላይ በጌታ ፊት ስቀላቸው።”
ይህም የሚሆነው፥ ዛሬ እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ከጠበቅህ፥ በጌታ በአምላክህ ፊት ትክክል የሆነውን ካደረግህ፥ የጌታ የአምላክህን ቃል ከሰማህ ነው።”
ይወድድህማል፥ ይባርክህማል፥ ያበዛህማል፤ ይሰጥህም ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የሆድህን ፍሬ እንዲሁም የምድርህንም ፍሬ፥ እህልና ወይንህን፥ ዘይትህንም፥ በከብትም ብዛት በበግም መንጋ አብዝቶ ይባርክልሃል።
እናንተ ግን እርም ካደረጋችሁት በኋላ እርም ከሆነው ነገር ራሳችሁን ጠብቁ፤ እርም ከሆነው አንዳች የወሰዳችሁ እንደሆነ የእስራኤልን ሰፈር የተረገመ ታደርጉታላችሁ፥ ታስጨንቁታላችሁም።
ከተማይቱንም በእርሷም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፤ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን የናሱንና የብረቱንም ዕቃ ብቻ በጌታ ግምጃ ቤት አኖሩት።
በዚያን ጊዜም ኢያሱ እንዲህ ብሎ ማለ፦ “ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በጌታ ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይጥፋ፥ በርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይጥፋ።”
የእስራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ነገር በደሉ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ፤ የጌታም ቁጣ በእስራኤል ልጆች ላይ ነደደ።
በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩ፤ ጌታም ከጽኑ ቁጣው ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ተጠራ።