አሞጽ 8:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በዚያ ቀን ቆነጃጅት ድንግሎችና ጉልማሶች በጥም ይዝላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ቀን፣ “ቈነጃጅት ሴቶችና ብርቱዎች ጕልማሶች፣ ከውሃ ጥም የተነሣ ይዝላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ቆነጃጅት ልጃገረዶችና ጠንካራ ወንዶች ወጣቶች እንኳ ከመጠማት የተነሣ ይዝላሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ቀን መልከ መልካሞቹ ደናግልና ጐበዛዝቱ በጥም ይዝላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ቀን መልካካሞች ደናግል ጐበዛዝትም በጥም ይዝላሉ። |
እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾህንና ኩርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነዳል፤ ጢሱም ተትጐልጉሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።
ጻዴ። በአፉ ነገር ላይ ዓመጽ አድርጌአለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ እባካችሁ፥ ስሙ መከራዬንም ተመልከቱ፥ ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ ተማርከው ሄዱ።
ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፥ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፥ የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ።
አለበለዚያ ዕራቁትዋን እንድትሆን እገፍፋታለሁ፥ እንደ ተወለደችበትም ቀን አደርጋታለሁ፥ እንደ ምድረ በዳና እንደ ደረቅ ምድር አደርጋታለሁ፥ በጥምም እገድላታለሁ።