2 ሳሙኤል 7:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናታንም ይህንን ቃል በሙሉ፥ ይህንንም ራእይ በሙሉ ለዳዊት ነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናታንም የዚህን ራእይ ቃል በሙሉ፣ ለዳዊት ነገረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ቃልና ራእይ ሁሉ መሠረት ናታን ለዳዊት ገለጠለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደዚህ ቃል ሁሉ፥ እንደዚህም ራእይ ሁሉ ናታን ለዳዊት እንዲሁ ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደዚህ ቃል ሁሉ እንደዚህም ራእይ ሁሉ ናታን ለዳዊት ነገረው። |
ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባ፤ በጌታ ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከዚህ ያደረስኸኝ ኧረ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድንነው?