2 ነገሥት 14:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሬሳውም በፈረስ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘውም የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስከሬኑን በፈረስ ጭነው አመጡ። እንደ አባቶቹም ሁሉ በዳዊት ከተማ፣ በኢየሩሳሌም ተቀበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሬሳውም በፈረስ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘውም የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድኑንም በፈረስ ጭነው አመጡት፤ በኢየሩሳሌምም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፈረስም ጭነው አመጡት፤ በኢየሩሳሌምም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ። |
አሜስያስን ለመግደል በኢየሩሳሌም ሤራ ተጠንስሶ ነበር፤ ስለዚህ አሜስያስ ሸሽቶ ወደ ላኪሽ ከተማ ሄደ፤ ነገር ግን ጠላቶች ወደ ላኪሽ ሰዎችን ልከው እዚያ አስገደሉት።
መንገሥም በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ሁለት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያዝንለት ከዚህ ዓለም በሞት ተሰናበተ፤ በዳዊትም ከተማ እንጂ በነገሥታቱ መቃብር አልቀበሩትም።
ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ እነርሱም፦ “ለምጻም ነው” ብለው ከአባቶቹ ጋር በነገሥታቱ መቃብር እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።