2 ዜና መዋዕል 31:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቅያስም በጌታ ቤት ውስጥ ግምጃ ቤት እንዲያዘጋጁ አዘዘ፤ እነርሱም አዘጋጁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ጐተራ እንዲያዘጋጁ አዘዛቸው፤ እነርሱም አዘጋጁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሕዝቅያስም በቤተ መቅደሱ አካባቢ የዕቃ ግምጃ ቤት እንዲዘጋጅ፥ አዞ በተዘጋጀ ጊዜ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቅያስም ለእግዚአብሔር ቤት ጎተራ ያዘጋጁ ዘንድ አዘዘ፤ እነርሱም አዘጋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር ቤት ጎተራ ያዘጋጁ ዘንድ አዘዘ፤ እነርሱም አዘጋጁ። |
ተጨማሪ ሆኖ የተሠራው ሕንጻ የታችኛው ፎቅ መግቢያ በር የሚገኘው ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ በኩል ነበር፤ እርሱም ከሁለተኛውና ከሦስተኛው ፎቅ ጋር የሚያገናኙት ደረጃዎች ነበሩት።
ትልቅ ለሌዋውያን፥ ለመዘምራን፥ ለበረኞቹ እንደ ሕጉ የተሰጣቸውን የእህሉን ቁርባንና ዕጣኑን፥ ዕቃዎቹንም፥ የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም አሥራት፥ ለካህናቱም የሆነውን የማንሣት ቁርባን አስቀድሞ ያስቀመጡበትን ታላቁን ጓዳ አዘጋጅቶለት ነበር።