2 ዜና መዋዕል 26:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ዓዛርያስ ከእርሱም ጋር ጽኑዓን የነበሩ ሰማኒያ የጌታ ካህናት ተከትለውት ገቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም ዓዛርያስ ቈራጥ ከሆኑ ከሌሎች ሰማንያ የእግዚአብሔር ካህናት ጋራ ተከትሎት ገባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ካህኑ ዐዛርያስና ከእርሱም ጋር ልበ ሙሉና ቈራጥ የሆኑ ሰማኒያ ካህናት ድርጊቱን ለመቃወም ንጉሡን ተከትለው ወደ ቤተ መቅደሱ ገቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ዓዛርያስ፥ ከእርሱም ጋር ጽኑዓን የነበሩ ሰማንያ የእግዚአብሔር ካህናት ተከትለው ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ዓዛርያስ ከእርሱም ጋር ጽኑአን የነበሩ ሰማኒያ የእግዚአብሔር ካህናት ተከትለው ገቡ። |
ንጉሡንም ዖዝያንን እየተቃወሙ እንዲህ አሉት፦ “ዖዝያን ሆይ! ዕጣን ማጠን የተቀደሱት የአሮን ልጆች የካህናቱ ሹመት ነው እንጂ ለጌታ እንድታጥን ለአንተ አይገባህም፤ በድለሃልና ከመቅደሱ ውጣ፤ ከአምላክህም ከጌታ ዘንድ ክብር አያስገኝልህም።”