1 ሳሙኤል 14:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፥ “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከልም ዕጣ ጣሉ” አላቸው። ዕጣውም በዮናታን ላይ ወደቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከልም ዕጣ ጣሉ” አላቸው። ዕጣውም በዮናታን ላይ ወደቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሳኦል “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከል ዕጣ ጣሉ” አለ፤ ዕጣውም በዮናታን ላይ መጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፥ “በእኔና በዮናታን መካከል ዕጣ አጣጥሉን፤ እግዚአብሔር ዕጣ ያወጣበትም ይሞታል” አላቸው። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “እንዲህ ያለ ነገር አይሆንም” አሉት፤ ሳኦልም ሕዝቡን እንቢ አላቸው። በእርሱና በልጁ በዮናታን መካከልም ዕጣ አጣጣሉ። ዕጣውም በልጁ በዮናታን ላይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፦ በእኔና በልጄ በዮናታን መካከል ዕጣ ጣሉ አለ። ዮናታንም ተያዘ። |
እርስ በእርሳቸውም፦ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደመጣብን እንድናውቅ ኑ፥ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፥ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።
ከዚያም ሳኦል ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ነገር ንገረኝ” አለው። ዮናታንም፥ “በበትሬ ጫፍ ጥቂት ማር ቀምሻለሁ፤ እነሆኝ፥ ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለው።