እርሷም፥ “ደም ተበቃዮቹ ተጨማሪ ደም እንዳያፈሱ ልጄም እንዳይገደል፥ ንጉሡ ጌታ አምላኩን ያስብ” አለች። ንጉሡም፥ “ሕያው በሆነው ጌታ እምላለሁ! ከልጅሽ አንድ ጠጉር በምድር ላይ አይወድቅም” አላት።
1 ነገሥት 1:52 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም፦ “እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጉር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም፥ ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደሆነ ይሞታል” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞንም፣ “አካሄዱን ካሳመረ ከራስ ጠጕሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም፤ ጥፋት ከተገኘበት ግን ይሞታል” ሲል መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሰሎሞንም “አካሄዱን ካሳመረ ከራስ ጠጒሩ አንዲት እንኳ አትነካበትም፤ ክፉ ሆኖ ከተገኘ ግን ይሞታል” ሲል መለሰ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም፥ “እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደ ሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጕር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም፤ ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደ ሆነ ይሞታል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም “እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደ ሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጕር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም፤ ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደ ሆነ ይሞታል፤” አለ። |
እርሷም፥ “ደም ተበቃዮቹ ተጨማሪ ደም እንዳያፈሱ ልጄም እንዳይገደል፥ ንጉሡ ጌታ አምላኩን ያስብ” አለች። ንጉሡም፥ “ሕያው በሆነው ጌታ እምላለሁ! ከልጅሽ አንድ ጠጉር በምድር ላይ አይወድቅም” አላት።
ለሰሎሞንም፦ “እነሆ፥ አዶንያስ ንጉሡን ሰሎሞንን ፈርቶ፦ ‘ንጉሡ ሰሎሞን ባርያውን በሰይፍ እንዳይገድለኝ ዛሬ ይማልልኝ’ ብሎ የመሠዊያውን ቀንድ ይዞአል” አሉት።
ሕዝቡ ግን ሳኦልን፥ “ለእስራኤል ይህን ታላቅ ድል ያስገኘ ዮናታን መሞት ይገባዋልን? ይህ አይሆንም! ዛሬ ይህን ያደረገው በእግዚአብሔር ርዳታ ስለ ሆነ፥ ሕያው ጌታን! ከራስ ጠጉሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም” አሉት። ስለዚህ ሰዎቹ ዮናታንን ታደጉት፤ እርሱም ከመሞት ዳነ።