1 ነገሥት 1:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ ዳዊትም ዕድሜው ገፍቶ ስለ ሸመገለ፥ ልብስ ደራርበው ቢያለብሱትም ሙቀት ሊሰጠው አልቻለም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ዳዊት እየሸመገለና ዕድሜው በጣም እየገፋ ሲሄድ፣ ልብስ ቢደራርቡለትም እንኳ ሊሞቀው አልቻለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዳዊት እጅግ ሸምግሎ ስለ ነበር አገልጋዮቹ የብርድ መከላከያ የሚሆን ልብስ ደራርበው ቢያለብሱትም ሙቀት ሊሰጠው አልቻለም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡ ዳዊትም አረጀ፤ ዘመኑም አለፈ፤ ልብስም ይደርቡለት ነበር፤ ነገር ግን አይሞቀውም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡ ዳዊትም ሸመገለ፤ ዕድሜውም በዛ፤ ልብስም ደረቡለት፤ ነገር ግን አይሞቀውም ነበር። |
በዚያም ዳዊት ለጌታ መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት አቀረበ። ከዚያም ጌታ ለምድሪቱ የቀረበውን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የመጣውም መቅሰፍት ቆመ።
ባርያዎቹም፦ “ንጉስ ሆይ! ከአንተ ጋር ሆና የምትንከባከብህ ወጣት ልጃገረድ ፈልገን እናምጣ፤ በጌታችንም በንጉሡ እቅፍ ተኝታ ታሞቅሃለች” አሉት።
ኢያሱም ሸመገለ ዕድሜውም ስለ ገፋ አረጀ፤ ጌታም እንዲህ አለው፦ “አንተ ሸምግለሃል፥ ዕድሜህም ስለ ገፋ አርጅተሃል፤ ያልተወረሰ እጅግ ብዙ ምድር ገና ይቀራል፤