1 ዜና መዋዕል 9:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንደሮቸቻቸውም የነበሩ ወንድሞቻቸው በየሰባትም ቀን ከእነርሱ ጋር አብረው ለመሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ይመጡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞቻቸውም በየመንደሮቻቸው ሆነው በየጊዜው እየወጡ የጥበቃውን ሥራ ሰባት ሰባት ቀን ያግዟቸው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህን ዘበኞች በመንደሮቻቸው የሚኖሩ ዘመዶቻቸው በየሰባቱ ቀን ተራ እየገቡ መርዳት ነበረባቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻቸውም በመንደሮቻቸው ሆነው፥ በየሰባቱ ቀን ከእነርሱ ጋር ሊሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይገቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቻቸውም በመንደሮቻቸው ሆነው፥ በየሰባትም ቀን ከእነርሱ ጋር ሊሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይገቡ ነበር። |
ሌዋውያንና ይሁዳም ሁሉ ካህኑ ዮዳሄ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ ካህኑም ዮዳሄ ሰሞነኞቹን አላሰናበተም ነበርና እያንዳንዱ በሰንበት ቀን ይገቡ የነበሩትን በሰንበትም ቀን ይወጡ የነበሩትን ሰዎች ወሰደ።