ዓዙባም ሞተች፥ ካሌብም ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሆርን ወለደችለት።
ዓዙባ ስትሞት፣ ካሌብ ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሑርን ወለደችለት።
ዐዙባ ከሞተችም በኋላ ካሌብ ኤፍራታ ተብላ የምትጠራ ሴት አግብቶ ሑር ተብሎ የሚጠራ ወንድ ልጅ ወለደ፤
ዐዙባም ሞተች፥ ካሌብም ኤፍራታን አገባ፤ እርስዋም ኦርን ወለደችለት።
ዓዙባም ሞተች፤ ካሌብም ኤፍራታን አገባ፤ እርስዋም ሆርን ወለደችለት።
የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባ ከይሪዖትም ልጆች ወለደ፤ ልጆቹዋም ያሳር፥ ሶባብ፥ አርዶን ነበሩ።
ሆርም ኡሪን ወለደ፥ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።
ኤስሮምም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮም ሚስት አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።
የካሌብ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የኤፍራታ የበኩሩ የሆር ልጅ የቂርያት-ይዓሪም አባት ሦባል፥
የጌዶርም አባት ፋኑኤል፥ የሑሻም አባት ኤጽር ነበር፤ እነዚህ የቤተልሔም አባት የኤፍራታ የበኩሩ የሆር ልጆች ናቸው።
ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴ፥ አሮንና ሑር ወደ ኮረብታው ጫፍ ወጡ።
ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ከዚህ በኋላ የቀሩት ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።