1 ዜና መዋዕል 17:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ስለ ባርያህ ስትል እንደ ልብህ ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ በማስታወቅ ይህን ተአምራት ሁሉ አድርገሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ባሪያህ ብለህና እንደ ፈቃድህም መሠረት ይህን ታላቅ ነገር አድርገሃል፤ እነዚህም ታላላቅ ተስፋዎች ሁሉ እንዲታወቁ አደረግህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ታደርግልኝ ዘንድ እንዲሁም ወደፊት ታላቅ እንደምታደርገኝ ታስታውቀኝ ዘንድ በጎ ፈቃድህና ዕቅድህ ሆኖአል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ልብህም ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ ለእኔ አደረግህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ! ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ ታስታውቀው ዘንድ ስለ ባሪያህ እንደ ልብህም ይህን ተአምራት ሁሉ አድርገሃል። |