ራጉኤልም ጦብያ መልአኩን እንደሚያነጋግረው ሰምቶ ጦብያን አነጋገረው፦ እንዲህም አለው፥ “አንድ ጊዜ ብላ፤ ጠጣ፤ ደስም ይበልህ፤
ከዚህ በኋላ ራጉኤል አንድ የበግ ሙክት አርዶ መልካም መስተንግዶ አደረገላቸው። ታጠቡና ለመብላት በማዕድ ተቀመጡ፥ ጦብያ ሩፋኤልን “ወንድሜ አዛርያ ዘመዴ የሆነችውን ሣራን እንዳገባ ራጉኤልን ጠይቀው” አለው።