Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽ​ሐፈ ጦቢት 7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


መል​አ​ኩና ጦብያ ወደ ራጉ​ኤል ቤት እንደ ደረሱ

1 ወደ ራጉ​ኤ​ልም ቤት ደረሱ፤ ሣራም ተቀ​ብላ ደስ አሰ​ኘ​ቻ​ቸው፤ እን​ዲሁ እነ​ር​ሱም እር​ሷን ደስ አሰ​ኙ​አት፤ ወደ ቤትም አስ​ገ​ባ​ቻ​ቸው።

2 ራጉ​ኤ​ልም ሚስቱ አድ​ናን፥ “ይህ ልጅ ድንቅ ነው፤ ከዘ​መ​ዶች ወገን የሆነ ጦቢ​ትን ይመ​ስ​ለ​ዋል” አላት።

3 ራጉ​ኤ​ልም፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን! እና​ንተ ከወ​ዴት ናችሁ?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “ወደ ነነዌ ከተ​ማ​ረ​ኩት ከን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች ነን” አሉት።

4 ራጉ​ኤ​ልም፥ “ወን​ድሜ ጦቢ​ትን ታው​ቁ​ታ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “እና​ው​ቀ​ዋ​ለን” አሉት። እር​ሱም፥ “በሕ​ይ​ወት አለን? ደኅና ነውን?” አላ​ቸው።

5 እነ​ር​ሱም፥ “አዎ ደኅና ነው” አሉት፤ ጦብ​ያም፥ “አባቴ ነው” አለው።

6 ራጉ​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ ሳመው፤ አለ​ቀ​ሰም።

7 “አንተ የደግ ሰው ልጅ ነህ” ብሎ መረ​ቀው፤ የጦ​ቢ​ትም ዐይ​ኖች እንደ ጠፉ ነገ​ረው። የጦ​ቢ​ትም ዐይ​ኖች እንደ ጠፉ በሰማ ጊዜ አዝኖ አለ​ቀሰ።

8 ሚስቱ አድ​ናና ልጁ ሣራም አለ​ቀሱ፤ በደ​ስ​ታም ተቀ​በ​ሉ​ዋ​ቸው፤ በግ አር​ደ​ውም፥ ማዕድ አቀ​ረ​ቡ​ላ​ቸው፤ እጅ​ግም መሸ። ጦብ​ያም አዛ​ር​ያን፥ “አንተ ወን​ድሜ አዛ​ርያ በጎ​ዳና ያል​ኸ​ኝን ነገር ተና​ገር፤ ነገ​ሩም ይለቅ፥” አለው።

9 ራጉ​ኤ​ልም ጦብያ መል​አ​ኩን እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ጋ​ግ​ረው ሰምቶ ጦብ​ያን አነ​ጋ​ገ​ረው፦ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አንድ ጊዜ ብላ፤ ጠጣ፤ ደስም ይበ​ልህ፤

10 ልጄ ለአ​ንተ ትገ​ባ​ለ​ችና፥ አን​ተም ታገ​ባ​ታ​ለ​ህና።

11 እኔም እው​ነ​ቱን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ ይህ​ችን ልጄን ለሰ​ባት ወን​ዶች አጋ​ባ​ኋት፤ ወደ እር​ሷም እንደ ገቡ በሌ​ሊት ይሞ​ታሉ፤ ነገር ግን አንድ ጊዜ ደስ ይበ​ልህ፤” ጦብ​ያም፥ “ነገ​ሩን ለኔ እስ​ክ​ት​ጨ​ር​ሱ​ልኝ ድረስ፥ ነገ​ሬ​ንም እስ​ክ​ታ​ጸ​ኑ​ልኝ ድረስ በዚህ ምንም አል​ቀ​ም​ስም” አለ።

12 ራጉ​ኤ​ልም አለው፥ “ከአ​ሁን ጀምሮ እንደ ሥር​ዐቱ ውሰ​ዳት፤ አንተ ወን​ድሟ ነህና፥ እር​ሷም እኅ​ትህ ናትና፤ ይቅር ባይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​በ​ጀ​ውን ያከ​ና​ው​ን​ላ​ችሁ።”

13 ልጁ ሣራ​ንም ጠራት፤ እጅ​ዋ​ንም ይዞ ሚስት ልት​ሆ​ነው ለጦ​ብያ ሰጣት፤ “እነሆ በሙሴ ሥር​ዐት ውሰ​ዳት፤ ወደ አባ​ት​ህም ቤት አግ​ባት” ብሎ መረ​ቃ​ቸው።

14 ሚስቱ አድ​ና​ንም ጠራት፤ ወረ​ቀ​ትም ወስዶ ጻፈና አተ​ማት።

15 ከዚ​ህም በኋላ ይበሉ ጀመሩ።

16 አድ​ና​ንም ጠርቶ፥ “አንቺ እኅቴ ሌላ የጫ​ጕላ ቤት አዘ​ጋጂ፤ ወደ​ዚ​ያም አግ​ቢ​ያት” አላት።

17 እን​ዳ​ላ​ትም አደ​ረ​ገች፤ ወደ​ዚ​ያም አገ​ባ​ቻት፤ አለ​ቀ​ሰ​ችም፤ የል​ጅ​ዋ​ንም እንባ ጠረ​ገች።

18 “ስለ​ዚች ኀዘ​ንሽ ፋንታ የሰ​ማ​ይና የም​ድር ጌታ ደስ​ታን እን​ደ​ሚ​ሰ​ጥሽ እመኝ” አለ​ቻት።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች