መዝሙር 52:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የግብዞችን አጥንቶች በትኖአልና በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅግ ፈሩ፤ እግዚአብሔር አዋርዶአቸዋልና አፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ያንኰታኵትሃል፤ ይነጥቅሃል፤ ከድንኳንህም መንጥቆ ያወጣሃል፤ ከሕያዋንም ምድር ይነቅልሃል። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥ ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዓመፃን ወደድህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለሙ ያጠፋሃል፤ ከቤትህ አስወጥቶ ያባርርሃል። ከሕያዋንም ምድር ያስወግድሃል። |
ደግሞም፦ በሕያዋን ምድር የእግዚአብሔርን ማዳን፤ የእስራኤልንም መዳን በምድር ላይ አላይም፤ ከዘመዶችም ሰውን አላይም።
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”