Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በማ​ኸ​ላት የዳ​ዊት መዝ​ሙር ፍጻሜ።

1 ሰነፍ በልቡ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለም ይላል። ረከሱ፥ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም ጐሰ​ቈሉ፤ በጎ ነገ​ርን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት የለም።

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ልግ አስ​ተ​ዋይ እን​ዳለ ያይ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ የሰው ልጆ​ችን ተመ​ለ​ከተ።

3 ሁሉ ተካ​ክሎ በአ​ን​ድ​ነት በደለ፤ አንድ ስንኳ በጎ ነገ​ርን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት የለም።

4 ሕዝ​ቤን እን​ጀ​ራን እንደ መብ​ላት የሚ​በሉ ግፍ አድ​ራ​ጊ​ዎች ሁሉ አያ​ው​ቁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አይ​ጠ​ሩ​ትም።

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ዞ​ችን አጥ​ን​ቶች በት​ኖ​አ​ልና በዚያ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ሳይ​ኖር እጅግ ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዋ​ር​ዶ​አ​ቸ​ዋ​ልና አፈሩ።

6 መድ​ኀ​ኒ​ትን ከጽ​ዮን ለእ​ስ​ራ​ኤል ማን ይሰ​ጣል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ዝ​ቡን ምርኮ በመ​ለሰ ጊዜ፥ ያዕ​ቆብ ደስ ይለ​ዋል እስ​ራ​ኤ​ልም ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች