ዘኍል 17:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴና አሮን ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገቡ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፤ ለመለመችም፤ አበባም አወጣች፤ የበሰለ ለውዝም አፈራች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገባ በሌዊ ቤት ስም የቀረበችው የአሮን በትር ማቈጥቈጥ ብቻ ሳይሆን እንቡጥ አውጥታ፣ አብባና አልሙን አፍርታ አገኛት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ በማግስቱ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነው የአሮን በትር አቈጥቁጦ፥ እምቡጥም አውጥቶ፥ አበባም አብቦ፥ የበሰለ ለውዝም አፍርቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ሙሴ ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ በሌዊ ነገድ ስም የቀረበችው የአሮን በትር ለምልማ አገኛት፤ ይኸውም እንቡጥ አውጥታ በማበብ የበሰለ የለውዝ ፍሬ አፍርታ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፥ ለመለመችም፥ አበባም አወጣች፥ የበሰለ ለውዝም አፈራች። |
በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በወንድሞች መካከል ነው። ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው።
በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከእስራኤል የተረፉትን ያከብርና ከፍ ያደርግ ዘንድ በጌትነቱ ምክር በምድር ላይ ያበራል።
የዱር ዛፎች ሁሉ፥ ረዥሙን ዛፍ ዝቅ ያደረግሁ፥ አጭሩንም ዛፍ ከፍ ያደረግሁ፥ የለመለመውንም ዛፍ ያደረቅሁ፥ የደረቀውንም ዛፍ ያለመለምሁ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናገርሁ፤ እኔም አደረግሁ።”
ነገር ግን በመዓት ተነቀለች፤ ወደ መሬትም ተጣለች፤ የሚያቃጥልም ነፋስ ፍሬዋን አደረቀ፤ ብርቱዎች በትሮችዋም ተሰበሩና ደረቁ፤ እሳትም በላቻቸው።
ከተመረጡት ጫፎችዋም በትር እሳት ወጣች፤ ፍሬዋንም በላች፤ የነገሥታትም በትር ይሆን ዘንድ የበረታ በትር የለባትም።” ይህ ሙሾ ነው፤ ለልቅሶም ይሆናል።
ለቆሬም ለማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አላቸው፥ “ነገ እግዚአብሔር የእርሱ የሚሆኑትን፥ ቅዱሳንም የሆኑትን ያያል፥ ያውቃልም፤ የመረጣቸውንም ሰዎች ወደ እርሱ ያቀርባቸዋል።
እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ትለመልማለች፤ በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁ የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።”
ሙሴም በትሮቹን ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ አወጣቸው፤ እነርሱም አዩ፤ እያንዳንዱም በትሩን ወሰደ።
በውስጥዋም የወርቅ ማዕጠንትና ሁለንተናዋን በወርቅ የለበጡአት፥ የኪዳን ታቦት፥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የለመለመችው የአሮን በትር፥ የኪዳኑም ጽላት ነበሩባት።